Main » 2014 » January » 2 » ወላይታ ሶዶ ከተማ
12:36 PM
ወላይታ ሶዶ ከተማ

  ወላይታ ሶዶ ከተማ የምትገኘዉ በደቡባዊ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት፣  በወላይታ ዞን፣ ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ በኩል በ390 ኪ.ሜና በሆሳእና በኩል 329 ኪ.ሜ፣ የደቡብ ክልል ርእሰ መዲና ከሆነችዉ ሀዋሳ ከተማ በ167 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡  ጂኦግራፊዊ አቀማመጧ  80 ሰሜን ላቲትዩድና 370  ምስራቅ ሎንጊቲዊድ ክልል ዉስጥ ነዉ፡፡

 

አመሠራረት

ወላይታ ሶዶ  ከተማ የተቆረቆረችው በ 1887 ነው፡፡ ከተማዋ የተመሰረተችዉ በወላይታ ንጉስ ጦናና በዓጼ ምኒሊክ ጦር

መካከል ለ7 አመታት ያህል ጦርነት ከተካሄደ በኋላ የዓጼ ምኒሊክ ማእከላዊ አስተዳደር በወላይታ ሲቋቋም በወቅቱ

የወላይታ አዉራጃ ዋና ከተማ እንድትሆን ነዉ፡፡  በኋላም  ደጃዝማች መኮንን ወሰኔ  የተባሉት በወቅቱ የወላይታ አዉራጃ

አስተዳዳሪ የነበሩት በ1924 ዓ/ም የአዉራጃዋ ከተማ ከዚህ ቀደም የንጉስ ጦና ቤ/መንግስት መቀመጫ ወደሆነዉና በአሁኑ

ወቅት ከሶዶ ከተማ በስተሰሜን ም. አቅጣጫ በ5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኘዉ አካባቢ በማዛወር የከተማዋንም ስም 

ዓለም ገነት ብለዉ የሰየሙ ሲሆን በ1928 የፋሽስት ጣልያን ጦር አገራችንን በወረሩበት ወቅት ተመልሶ ከተማዋ  አሁን

በምትገኝበት በቀድሞዋ ቦታ እንድትከትም ተደረገ፡፡

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የከተማዋ ስያሜ የመጣዉ ከ150 አመታት በፊት በአካባቢዉ ይኖሩ ከነበሩ ታዋቂ

ነጋዴ ከነበሩት ሞቼና ቦራጎ ሶዶ ነዉ፡፡ እንደ ሌሎች ምንጮች ደግሞ ከተማዋ ስያሜ የመጣዉ አሁን ከተማዋ  በምትገኝበት

አቅራቢያ ከነበረዉ ሶዷ ሹቻ (የሶዶ ድንጋይ) ከሚባል ትልቅ የድንጋይ አለት ጋር በተያያዘ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ብዙዎቹ 

የሚስማሙበት የከተማዋ ስያሜ አመጣጥ በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰዉ ነዉ፡፡ወላይታ ሶዶ  በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም  ከተሞች አንድዋ ስትሆን የከተማ አስተዳደር፣ ሶስት ክ/ከተሞችና 11 ቀበሌዎች 

አሷት፡፡ በከተማዋ አስተዳደራዊ የሆኑ ስራዎች የሚመሩት በከተማዉ አስተዳደር በተቋቋመዉ የከንቲባ ጽ/ቤት ሲሆን 

የከተማ አገልግሎት ስራዎች የሚመሩት  በስራ አስኪያጅ የሚተዳደር የከተማ ማዘጋጃ ቤት ነዉ፡፡ በ1999 ዓ.ም የተዘጋጀ

መዋቅራዊ ፕላን አላት፡፡
Attachments: Image 1
Views: 1930 | Added by: Temesgen_w | Rating: 2.3/3
Total comments: 0
Name *:
Email *:
Code *: